ኢትዮጵያ ሊቢያ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል እንድትሆን ድጋፏን መስጠቷ ተዘገበ
15:40 30.09.2026 (የተሻሻለ: 15:44 30.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሊቢያ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል እንድትሆን ድጋፏን መስጠቷ ተዘገበ
ኢትዮጵያ በትሪፖሊ በተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚቴ የባለሙያዎች ስብሰባ ላይ፤ ሊቢያ ለፈረንጆቹ 2028-2029 ዘመን ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ግዜያዊ ወንበር ያቀረበችውን ዕጩነት እንደምትደግፍ ይፋ ማድረጓን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
አዲስ አበባ የትሪፖሊን የጸጥታው ምክር ቤት አባልነት ጥያቄ መደገፏን ያረጋገጠችው በሊቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር አሽራፍ ሞሐመድ አል-ታይብ እና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ዘሪሁን አበበ በመሩት የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ሁለተኛው የኢትዮጵያ እና ሊቢያ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ እ.አ.አ. በ2027 የመጀመሪያ አጋማሽ በትሪፖሊ እንዲካሄድ እና በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች እንዲፈረሙ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
