ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ስርዓትን ተካፈሉ
15:01 30.09.2026 (የተሻሻለ: 15:04 30.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ስርዓትን ተካፈሉ
የኢትዮጵያው መሪ፣ በኬንያ ላሙ ወደብ በ2.2 ትሪሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (16 ቢሊዮን ዶላር) ኢንቨስትመንት የሚገነባው የዳንግቴ ምስራቅ አፍሪካ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓትን ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ከሌሎች የቀጣና ሀገራት መሪዎች ጋር ተሳትፈዋል፡፡
ስለ ፕሮጀክቱ ዋና ዋና መረጃዎች፦
▪ የኢንቨስትመንት መጠን፦16 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው።
▪ የማጣራት አቅም፦ በቀን 700,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ያጣራል።
▪ የሥራ ዕድል፦ ለ60,000 የኬንያ ወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
▪ የኃይል ዋስትና፦ ለምሥራቅና ማዕከላዊ አፍሪካ 8 ገበያዎች የኃይል ዋስትና ይሰጣል።
በሥነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ መሪዎችና እንግዶች፦
ዊሊያም ሩቶ – የኬንያ ፕሬዝዳንት
ዐቢይ አሕመድ – የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር
ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ – የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት
ሮሙዋልድ ዋዳግኒ – የቤኒን ፕሬዝዳንት
ዣን-ሉሲያን ሳቪ ዲ ቶቬ – የቶጎ ፕሬዝዳንት
ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ – የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት
የሌሎች አፍሪካ ሀገራት መንግሥታት ተወካዮች
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
