የስንዴ ራስ አድረቅ በሽታ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፤ ቀጣናዊ ቅንጅት ያስፈልገዋል – ተመራማሪ
20:50 29.09.2026 (የተሻሻለ: 20:54 29.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የስንዴ ራስ አድረቅ በሽታ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፤ ቀጣናዊ ቅንጅት ያስፈልገዋል – ተመራማሪ
ከዚህ ቀደም ለብዙ ዓመታት የስንዴ ምርትን ሲጎዱ ከቆዩት የግንደ ዝገት (ዋግ) እና ቢጫ ዝገት (ዋግ) በሽታዎች በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት "የስንዴ ራስ አድረቅ" የተባለው በሽታ የበለጠ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የምስራቅ አፍሪካ የስንዴ ምርምር ማዕከል ተመራማሪ ዶ/ር ዘሪያሁን ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገለጹ።
“በሽታው በብዙ ሺህ ሄክታር ላይ የሚገኝ እና የአርሶ አደሩን በሽታ የመቋቋም አቅም እየተፈታተነ ይገኛል።”
ባለሙያው ትኩረቱን በስንዴ በሽታዎች ላይ አድርጎ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስተናጋጅነት ከተካሄደው ዐውደ-ጥናት ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ በሽታው በብዙ ሺህ ሄክታር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአርሶ አደሩን በሽታ የመቋቋም አቅም እየተፈታተነ ይገኛል።
▪ በሽታው በዋናነት ተክሉ ወደ ማሻት ደረጃ ሲደርስ የሚያጠቃ በመሆኑ በጸረ-ህዋሳት መድኃኒቶች ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል።
▪ ችግሩን ለመቋቋም የተቀናጀ የበሽታ አስተዳደር መከተል አስፈላጊ ነው።
▪ በሽታው ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ የአፍሪካ ሕብረት እና የደቡብ እስያ ሀገራት በትብብር መሥራት ይገባቸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X