የሩሲያው ሮሳቶም በማሊ ዐቢይ የሊቲየም ማዕድን ማውጫ ሊገነባ ነው - ዘገባዎች
20:40 29.09.2026 (የተሻሻለ: 20:44 29.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያው ሮሳቶም በማሊ ዐቢይ የሊቲየም ማዕድን ማውጫ ሊገነባ ነው - ዘገባዎች
በደቡብ-ምዕራብ ማሊ በሚገኘው ቡጉላ የማዕድን ስፍራ ላይ የሚደረገው ማውጫ ግንባታ እ.ኤ.አ በ2028 ይጀመራል ሲሉ የፕሮጀክቱ መሪ አንድሬ ሚኔቭ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ሰፊ የአሰሳ ሥራ ቦታው ለዓለም አቀፉ የባትሪ ኢንዱስትሪ ዋና ጥሬ ዕቃ የሆነው የስፖዱሜን ኮንሰንትሬት ከፍተኛ እምቅ አቅም እንዳለው ማረጋገጡን ገልጸዋል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
▪ የማዕድን ክምችት፦ 458,000 ቶን ሊቲየም ካርቦኔት
▪ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ሚና፦ ይህ የማዕድን ክምችት ፈጣን እድገት እያሳየ ያለውን የሊቲየም ፍላጎት ለማሟላት፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እና የታዳሽ ኃይል ማከማቻ ሥርዓቶችን ለማንቀሳቀስ እጅግ አስፈላጊ ነው።
▪ ለሕብረተሰቡ የተሰጠ ትኩረት፦ ፕሮጀክቱ የአካባቢው ተወላጆችን በሥራ እድል ቅጥር ማስቀደም፣ በሁሉንም አየር ሁኔታ የሚያገለግሉ መንገድዎችን መገንባት እና በቡጉላ መንደር ለሚኖሩ ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብን ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርጎታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X