በኢትዮጵያ 20 በመቶ የሚሆኑ አባወራዎች ቢያንስ አንድ ኣካል ጉዳተኛ የቤተሰብ አባል አላቸው - ጥናት
19:25 29.09.2026 (የተሻሻለ: 19:34 29.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ 20 በመቶ የሚሆኑ አባወራዎች ቢያንስ አንድ ኣካል ጉዳተኛ የቤተሰብ አባል አላቸው - ጥናት
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከዩኬ ኤይድ እና ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በ12 ክልሎች እና 2 የከተማ አስተዳደሮች፤ 9,200 አባወራዎችንና 42,264 ግለሰቦችን በማካተት በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ያካሄደው ሀገራዊ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ይፋ ሆኗል።
በጥናቱ ከተካተቱት አጠቃላይ አባወራዎች ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት (በገጠር 22%፣ በከተሞች 17%) ቢያንስ አንድ የአካል ጉዳት ያለበት የቤተሰብ አባል እንዳላቸው ተመላክቷል።
ከፍተኛ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር የያዙ ክልሎች፦
🟠 ትግራይ፦ 30%
🟠 አማራ፦ 25.8%
🟠 ጋምቤላ፦ 22%
🟠 ሱማሌ፦ 22%
የአካል ጉዳት ዋና ዋና መንስኤዎች
🟠ሕመም፦ 51%
🟠ግጭት፣ አደጋዎችና ቁስለቶች፦ 13%
🟠በውል የማይታወቁ ምክንያቶች፦ 11%
🟠እርጅና፦ 7%
አካል ጉዳተኛ ከሆኑት ሴቶች መካከል 35% ያህሉ ብቻ የሥራ እድል ሲኖራቸው፣ 65% የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት የሥራ ዕድል እንዳላገኙ ጥናቱ አመላክቷል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X