በሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባን ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚዎች ይኖራሉ – የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን
18:15 29.09.2026 (የተሻሻለ: 19:24 29.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባን ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚዎች ይኖራሉ – የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን
ኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ከሩሲያ ጋር ቀደም ሲልም በርካታ የባህል ልውውጦችን እያደረጉ መቆየታቸውን የገለፁት የኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ልደት ሙለታ አሁንም በርካታ የባህል ልውውጦች አሉን ብለዋል።
“በቀጣይም የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ እንደሚካሄድ ይታወቃል፤ በዚሁ ጉባኤ ወቅት ወይም ከዚያ በፊት አዲስ አበባን ለማስተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚዎች ይኖራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እንደመሆናችን መጠን፣ የባህል ዝግጅት ይሁን የክልል ስብሰባ ወይም የብሪክስ ስብሰባ፣ ማንኛውንም ዕድል በመጠቀም አዲስ አበባን ለማስተዋወቅ እንተጋለን።”
አዲስ አበባ ቀዳሚ የስብሰባ፣ የማበረታቻ፣ የኮንፈረንስ እና የዐውደ–ርዕይ (የማይስ) ማዕከል ማድረግን አስመልክቶ ከስፑትኒክ አፍሪካ ባደረጉት ቃለመጠይቅ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች በስፑትኒክ አፍሪካ ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡
የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጥቅምት 18 እና 19 በሞስኮ ይካሄዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X