- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ከአፍሪካ ወሰን ባሻገር፡ የስደት ፖሊሲዎችን ማን፣ ለምን ይቀርጻል?

ከአፍሪካ ወሰን ባሻገር፡ የስደት ፖሊሲዎችን ማን፣ ለምን ይቀርጻል?
ሰብስክራይብ
የአውሮፓ ሀገራት የስደት እና የድንበር ፖሊሲ ድንበራቸውን በራሳቸው አካባቢ ብቻ የሚገድብ ሳይሆን፣ ስደትን ከመነሻው እና ከመሸጋገሪያ ሀገራት ጀምሮ ሄዶ መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው።
“አውሮፓ ሀገራት የውጪ ድንበራቸውን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት የስደት ቁጥጥር ፖሊሲያቸው በአፍሪካ መነሻ እና መሸጋገሪያ ሀገራት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ስደትን ከምንጩ ለመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ነው [...] አውሮፓውያን በስደት ቁጥጥር ሰበብም የአፍሪካውያን ፖሊሲዎች [የፍልሰት] ቀረፃ ሂደት ላይ ጫና ያሳድራሉ” ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ሜሮን ዘለቅ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት፤ በአፍሪካ እና በአውሮፓ መካከል ስላለው የስደት አስተዳደር፣ አህጉራዊ አቅጣጫዎች፣ የሉዓላዊነት ተግዳሮቶች፣ እንዲሁም የሰለጠነ ሰውኃይል ፍልሰት ላይ ሰፊ ዳሰሳ እናደርጋለን። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ሜሮን ዘለቀ (ዶ/ር) ደግሞ እንግዳችን ናቸው።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0