አፍሪካ የሚያስፈልጋት የምዕራባውያን ምጽዋት ሳይሆን፥ ፍትሐዊ አጋርነት እና እንደ ብሪክስ ያሉ አማራጭ ወዳጆች ነው - ባለሙያው
አፍሪካ የሚያስፈልጋት የምዕራባውያን ምጽዋት ሳይሆን፥ ፍትሐዊ አጋርነት እና እንደ ብሪክስ ያሉ አማራጭ ወዳጆች ነው - ባለሙያው
ምዕራባውያን ምጽዋት እና እርዳታ የሚሉት ነገር በፍትሃዊ ያልሆነ ንግድ እና ብዝበዛ ከአፍሪካ ካጋበሱት ሀብት ጋር ሲነጻጸር እጅግ በጣም ትንሽ እጅ ነው ሲሉ የአፍሪካ ወጣቶች ለሰላምና ደህንነት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አብርሃም ኮርብላ ክሉትሴ የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንት ማሃማ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ያደረጉትን ንግግር አስመልክተው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ከክሉትሴ የተሰጡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 ብሪክስ እና አማራጮች፦ ብሪክስ፣ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና እና የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤዎች አፍሪካ ኢኮኖሚዋን እንድትገነባ እና ከምዕራባውያን ጋር በሚደረጉ ድርድሮች ላይ የመደራደር አቅሟን እንድታሳድግ የተሻሉ እድሎችን ያቀርባሉ።
🟠 የጋራ መገበያያ ገንዘብ ፦ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ለአፍሪካ ሀገራት የጋራ ገንዘብ ለመጀመር ሊረዳ ይችላል፤ በዚህም ሀገራቱ በአህጉሪቱ ቁጥጥር ስር ባልሆነው የአሜሪካ ዶላር እርስ በርሳቸው መነገዳቸውን ያቆማሉ።
🟠 ሩሲያ እንደ ታማኝ አጋር፦ ሞስኮ ከነፃነት ዘመን ጀምሮ በንግድ፣ በደህንነት እና በነፃነት ትግል ወቅት ወጥ የሆነች አጋር ሆና የቆየች ሲሆን "የገባችውን ቃል ኪዳንም አፍርሳ አታውቅም።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
