ኢትዮጵያ በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ስብሰባ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ገለፀች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ስብሰባ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ገለፀች

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በበይነ-መረብ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ፤ ኢትዮጵያ በበለፀገ እና በተሳሰረ ቀጣና የመገንባት ቁርጠኝነቷን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

"የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማደያ ቧንቧ መስመር ግንባታ እና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መግባት፣ ለቀጣናችን የነዳጅ ዋስትናን ለማረጋገጥና ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ወሳኝ ምዕራፎች ናቸው።" ብለዋል፡፡

አሕመድ ሽዴ፣ የቀጣናውን የኢነርጂ ትስስር ላይ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ የተጣሉባትን ግቦች ለማሳካት በጥሩ አካሄድ ላይ እንደምትገኝ አስረድተዋል፡፡

"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ደረጃ የሚካሄዱ የንግድ ማመቻቸትና የኢነርጂ ትስስር ሥራዎችን በግንባር ቀደምትነት የመደገፍና የተጣሉባትን ግቦች በውጤታማነት የማሳካት ቁርጠኝነቷ የጸና ነው።"

በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተደረሱ ስምምነቶች እና የክልላዊ ንግድ ማመቻቸት ኮሚቴ መቋቋም ድጋፍ እንደተደረገለትም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0