ጋና በታሪኳ ግዙፉን የጋዝ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት እንዳቀደች ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ጋና በታሪኳ ግዙፉን የጋዝ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት እንዳቀደች ፕሬዚዳንቱ ተናገሩ

መንግሥት እ.ኤ.አ እስከ 2026 መጨረሻ ድረስ 1,200 ሜጋ ዋት የሚያመነጭና በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደር በጋዝ የሚሠራ የሙቀት ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ለመፈረም ማቀዱን ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ በኒውዮርክ ከሚኖሩ የጋና ማኅበረሰብ አባላት ጋር ባደረጉት ሕዝባዊ ውይይት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፦

▪ የኃይል ማመንጫው መስፋፋት በኃይል አቅርቦት ለውጥ የሚመጣ የሃብት መባከንን ለማስቀረት መንግሥት ከሚከተለው የታዳሽ ኃይል ሽግግር ጋር የተጣጣመ ነው።

▪ መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማረጋጋት የኃይል ዘርፉን ዕዳዎች የከፈለ ሲሆን የጋና ኤሌክትሪክ ኩባንያንም ዳግም አደራጅቷል።

▪ ማሃማ የታቀደውን የሙቀት ኃይል ማመንጫ በጋና የኃይል ዘርፍ ከተነሳሳው አዲስ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጋር አያይዘውታል። የሀገሪቱ የነዳጅ ምርት በ2 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ታግዞ እ.ኤ.አ ከ2025 ወዲህ በ38% አድጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0