የተመድ መሪ ቃል ሥርዓታዊ በደል እንዳለ በመቀበሉ፤ ቡርኪና ፋሶ የሀገራት እኩል ልዑላዊነት እንዲከበር ትጠይቃለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የተመድ መሪ ቃል ሥርዓታዊ በደል እንዳለ በመቀበሉ፤ ቡርኪና ፋሶ የሀገራት እኩል ልዑላዊነት እንዲከበር ትጠይቃለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

“እምነትን መገንባት፣ ለውጥን መምራት፦ ለሁሉም የሚሠራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት” የሚለው መሪ ቃል በአባል ሀገራት መካከል የእምነት መሸርሸር፣ ወገንተኝነት እና ሥርዓታዊ ፍትሕ መጓደል መኖሩን የሚቀበል ነው ሲሉ የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካራሞኮ ዣን-ማሪ ትራኦሬ በ81ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።

 

“የበላይነት፣ ሥርዓት አልበኝነት እና ላዕላይነት ዝንባሌያቸው ግልጽ በሆነ አባል ሀገራት ምክንያት ዓለም አቀፍ ሕግ እየተጣሰና እየተገፋ ይገኛል” ብለዋል።

ተመድ “በክብር፣ በመብትና በልዑላዊነት እኩል የሆኑ የሁሉም ሕዝቦች የጋራ ቤት” መሆን አለበት ሲሉም ሚኒስትሩ አጽንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0