ጥሩ አሸባሪ እና መጥፎ አሸባሪ የሚባል ነገር የለም - ማሊ ዓለም አቀፋዊውን ስጋት በኅብረት ለመዋጋት ጥሪ አቀረበች
17:16 28.09.2026 (የተሻሻለ: 17:24 28.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጥሩ አሸባሪ እና መጥፎ አሸባሪ የሚባል ነገር የለም - ማሊ ዓለም አቀፋዊውን ስጋት በኅብረት ለመዋጋት ጥሪ አቀረበች
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር፤ ሽብርተኝነት ላይ የሚካሄደው ውጊያ ከቀጣናው ባሻገር ሰፊ አንድምታ ያለው "በውክልና የሚካሄድ ቅይጥ ጦርነት" እንደሆነ ገልጸዋል።
የማሊ ኃይሎች በተናጠልም ሆነ በሳኀል ሀገራት የጋራ ኃይል ሥር፤ ከተጫነባቸው ሽብርተኝነት ጋር በግንባር ቀደምትነት እየተዋጉ እንደሚገኙና ለዚህም ከሩሲያ ፌዴሬሽን ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አብራርተዋል።
ሦስቱ የሳኅል አባል ሀገራት ልዑላዊነታቸውን፣ የግዛት አንድነታቸውን፣ ስትራቴጂካዊ ምርጫዎቻቸውን እና የሕዝቦቻቸውን ጥቅም ከሚያከብሩ አጋሮች ጋር ለመተባበር ዝግጁ እንደሆኑ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
