ኢትዮጵያ የባቡር መገጣጠሚያ ማዕከል ግንባታ እና የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር ማሻሻያ ዕቅድ ይፋ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ የባቡር መገጣጠሚያ ማዕከል ግንባታ እና የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር ማሻሻያ ዕቅድ ይፋ አደረገች
ኢትዮጵያ የባቡር መገጣጠሚያ ማዕከል ግንባታ እና የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር ማሻሻያ ዕቅድ ይፋ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.09.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የባቡር መገጣጠሚያ ማዕከል ግንባታ እና የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመር ማሻሻያ ዕቅድ ይፋ አደረገች

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከህንዱ ፊዛ ኤሊክሰር ኢንፍራስትራክቸር ኩባንያ ጋር የባቡር እና የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ፕሮጀክቶችን ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

የስምምነቱ ቁልፍ ትኩረቶች፦

በኮምቦልቻ ወርክሾፕ የባቡር ጥገና፣ የመለዋወጫ እቃዎችና የባቡር አካላት ማምረቻ ማዕከል ማቋቋም፣

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ቲኬቲንግ ሥርዓት ማሻሻል፣

ተጨማሪ ባቡሮችን ማቅረብ፣

የኤሌክትሪክ፣ የሲግናልና የኮሙኒኬሽን ሥርዓቶች ማዘመን።

ስምምነቱ የኢትዮጵያን የባቡርና የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመን፣ የሀገር ውስጥ ምርት ለማሳደግ እና ዘላቂ የልማትና የንግድ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያግዝ የትብብር መሠረት ይፈጥራል ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0