የህዋ ትብብር በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጥ አይቆምም – የሩሲያ ጠፈርተኛ
17:56 26.09.2026 (የተሻሻለ: 18:04 26.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የህዋ ትብብር በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጥ አይቆምም – የሩሲያ ጠፈርተኛ
በሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቢቋረጥም የህዋ ትብብር እንደሚቀጥል ሩሲያዊው ጠፈርተኛና የሩሲያ ጀግና የክብር ማዕረግ ባለቤት ዬቭጄኒ ታሬልኪን ገልጸዋል።
ታሬልኪን ይህን ያሉት በቭላዲሚር ከተካሄደው የሰላማዊ የህዋ ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው።
“በህዋ ዘርፍ ሁሌም የግንኙነት መስመሮች ይኖራሉ፤ በእርግጥም የህዋ ትብብር በአብዛኛው በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች መሻከር አይጎዳም” ብለዋል።
የዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ አባላት እንደ “አንድ አካል” ሆነው እንደሚሠሩ የገለጹት ታሬልኪን፤ የፖለቲካ ልዩነቶች በህዋ ሥራ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እንደማይገባ አስገንዝበዋል።
“አንድ የቡድኑ አካል አንድ ሀገር ላይ ባለ ቂም ወይም በሌላ ምክንያት ሥራውን በአግባቡ ማከናወን ቢያቆም፤ ሰዎች ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ታሬልኪን ህዋን ወደ ወታደራዊ ውድድር መስክ ለመቀየር የሚደረጉ ጥረቶችንም ተችተዋል።
“አሁን አንዳንዶች ዳግም ህዋን ወታደራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፤ ይህ ግን ትክክል አይደለም” ብለዋል።
የ “ጎልደን ዶም” ፕሮጀክቶችን ጨምሮ አሜሪካ ህዋን ለወታደራዊ ዓላማ ለማዋል የምታደርገው ጥረት፤ የህዋ ትብብርንና ዓለም አቀፍ መረጋጋትን ከመጉዳት ባለፈ በህዋ ላይ ያለውን የኃይል ሚዛን ሊያዛባ እንደሚችል ታሬልኪን አስገንዝበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
