"ጎልደን ዶም" የህዋ የኃይል ሚዛንን ያዛባል - የሩሲያ ባለሥልጣን
16:38 26.09.2026 (የተሻሻለ: 16:58 26.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"ጎልደን ዶም" የህዋ የኃይል ሚዛንን ያዛባል - የሩሲያ ባለሥልጣን
አሜሪካ "ጎልደን ዶም" የተሰኘውን ስትራቴጂካዊ ሥርዓት ለመዘርጋት የምታደርገው ጥረት፤ የህዋን መረጋጋት እና የኃይል ሚዛን የሚያናጋ ስጋት ደቅኗል ሲሉ የቭላዲሚር ክልል የሕግ መወሰኛ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ቪያቼስላቭ ካርቱክሂን ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ ይህን ያሉት በቭላዲሚር ከተካሄደው የሰላማዊ ህዋ ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው።
ካርቱክሂን “የአሜሪካን ስትራቴጂካዊ የጎልደን ዶም ሥርዓት የመጀመር እንቅስቃሴ ልንጋራው አንችልም” ብለዋል።
የዋሽንግተን ፕሮጀክት ከሰላማዊ የህዋ ምርምር መርህ ጋር እንደሚቃረንም አስጠንቅቀዋል።
“ይህ ስርዓት በህዋ ላይ ያለውን መረጋጋት እና የኃይል ሚዛን ሊያዛባ ይችላል፤ ይህም በእኛ እይታ ለሰላማዊ የህዋ ምርምር አስተዋፅኦ አያደርግም።”
በህዋ ላይ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከወታደራዊ ውድድር ይልቅ ዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም አስምረዋል።
“በመጀመሪያ ደረጃ ዓለም አቀፍ ሕግ በህዋ ላይ እንዲከበር ጥረታችንን ማቀናጀት አለብን፤ ምክንያቱም ሁሉም ነገር በአንድ ቅጽበት ሊወድም ይችላል።”
ካርቱክሂን በተጨማሪም ሩሲያና ቻይና እስካሁን የራሳቸውን ሳተላይት ወይም ጠፈርተኞችን ወደ ህዋ ያልላኩ ሀገራትን ማገዝ እንደሚችሉ ገልጸዋል። ህዋ አሜሪካ እንደምታደርገው የወታደራዊ ውድድር ሳይሆን የትብብር መስክ ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X