የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ሁለት አዳዲስ የጤና ዞኖች መሠራጨቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
16:22 26.09.2026 (የተሻሻለ: 16:24 26.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢቦላ ወረርሽኝ ወደ ሁለት አዳዲስ የጤና ዞኖች መሠራጨቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
ወረርሽኙ ከሀገሪቱ 26 ግዛቶች ውስጥ በሰባቱ ተሠራጭቶ፤ በሽታው የተከሰተባቸው አጠቃላይ የጤና ዞኖች ቁጥር 63 መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት ዐርብ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
የቅርብ ጊዜ መረጃዎች፦
7,890 የተረጋገጡ ሕመምተኞች እና 3,799 ሞቶች፣
አጠቃላይ የሞት ምጣኔ 48.1%፣
ወረርሽኙ የደረሰባቸው አዲስ ዞኖች በሱድ ኡባንጊ ግዛት ቡሉን እና በኦት ኡኤሌ የሚገኘው ዱንጉን ናቸው፣
ኦት ኡኤሌ ከደቡብ ሱዳን ጋር ስለሚዋሰን ወረርሽኙ ድንበር የመሻገር ዕድሉ እየጨመረ መጥቷል።
ℹ ከፍተኛ ሆኖ የቀጠለው የሞት ምጣኔ የበሽታውን አሳሳቢነት እንዲሁም በወቅቱ በሽታውን መለየት እና ቅድመ ህክምና ችግር እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ይህም በቤተሰብ፣ በማኅበረሰብ እና በጤና ተቋማት ውስጥ ስርጭቱ እንዲቀጥል አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
