- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የእንስሳት ህክምና አድዋ፣ የሳይንሳዊ ሉዓላዊነት እና የቦቫይን ቲቢ (BTB) መቆጣጠሪያ ሀገር በቀል ስትራቴጂ

የእንስሳት ህክምና አድዋ፣ የሳይንሳዊ ሉዓላዊነት እና የቦቫይን ቲቢ (BTB) መቆጣጠሪያ ሀገር በቀል ስትራቴጂ
ሰብስክራይብ

ለአስርተ ዓመታት በአፍሪካ ላይ ሲተገበር የቆየውና እንስሳቱን አርዶ ማስወገድን የሚጠይቀው የምዕራባውያን 'መርምሮ ማረድ' (Test and Cull) ፖሊሲ፣ የታዳጊ ሀገራትን ነባራዊ ሁኔታና የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ያላገናዘበ ነበር። አሁን ግን ጥጆችን እንደተወለዱ ከታመመች እናት በመለየት፣ ወተትን በማፍላት እና ንክኪን በማስወገድ ያለምንም ውድ የመድኃኒት ግዢና የከብቶች እርድ በ3 ዓመታት ውስጥ እርባታን 100% ከበሽታ ነፃ የሚያደርግ ሀገር በቀል ስትራቴጂ እውን በማድረግ የሳይንስና የፖሊሲ ሉዓላዊነታችንን አረጋግጠናል፤'' ሲሉ

የኢትዮጵያ እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪው ዶ/ር ማቲዎስ ላቀው ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፖድካስት፤ የቀንድ ከብቶች የሳምባ ነቀርሳ (Bovine TB) በወተት እርባታ ዘርፍና በምግብ ዋስትና ላይ የሚያደርሰውን ከባድ ጉዳት፣ የምዕራባውያን ፖሊሲዎች በታዳጊ ሀገራት ለምን እንደከሸፉ፣ ያለምንም ተጨማሪ የመድኃኒት ወጪ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ የሚያድነው አዲሱ ሳይንሳዊ አሰራር አፈጻጸም፣ እንዲሁም የህብረተሰብ ጤናን በመጠበቅ አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል ሳይንስና ምርምር ችግሮቻቸውን የመፍታት አህጉራዊ አቅማቸውን በጥልቅ ዳስሰናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0