ላቭሮቭ የቡቻን "የፈጠራ ወሬ" የሚያጋልጥ ሪፖርት ለተመድ ዋና ፀሐፊ አስረከቡ፤ ዩክሬንን "የጆሴፍ ጎብልስ ወራሽ" ሲሉ ኮነኑ

ሰብስክራይብ

ላቭሮቭ የቡቻን "የፈጠራ ወሬ" የሚያጋልጥ ሪፖርት ለተመድ ዋና ፀሐፊ አስረከቡ፤ ዩክሬንን "የጆሴፍ ጎብልስ ወራሽ" ሲሉ ኮነኑ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴርጌ ላቭሮቭ፤ በቡቻ ከተማ ክስተት ዙሪያ የኪየቭን ትርከት የሚሞግት ሪፖርት ለተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አስረክበው፤ የድርጅቱ ሴክሬተሪያት ዝርዝር ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቀዋል።

"የጎብልስ ወራሾች፣ በቡቻ የቀነባበረው ሀሰት እና የኪየቭ አገዛዝ ደምና ድራማ” የሚል ርዕስ ያለው ይህ ሰነድ፤ ዩክሬን እና አጋሮቿ የኔቶ አባላት ክስተቶችን አቀናብሮ በማዘጋጀት እና የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ይከሳል።

የቡቻ "የፈጠራ ወሬ" እ.ኤ.አ በ2022 ከኪየቭ አቅራቢያ በሚገኝ ከተማ የተፈጠረውን ክስተት የሚመለከት ሲሆን የዩክሬን ታጣቂዎች ሩሲያን በ "ጦር ወንጀል" ለመክሰስ እና የሰላም ንግግር ለማስተጓጎል የገዛ ዜጎቻቸውን የጨፈጨፉበት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0