- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ስትራቴጂ

የሎጂስቲክስ ሉዓላዊነት፣ የዲጂታል መሠረተ ልማት እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ስትራቴጂ
ሰብስክራይብ

አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎቿን በቀጥታ ወደ ውጭ ለሚልኩ ኤክስፖርተሮች ብቻ የምታቀርብበት የተላላኪነት መዋቅር ውስጥ ተዘፍቃ ቆይታለች። አሁን ግን የሎጂስቲክስና የንግድ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ፣ የአፍሪካን ሀብት እዚሁ አህጉራችን ውስጥ እሴት በመጨመር ማቀናበር፣ የድንበር ላይ እንግልቶችን በዲጂታል ሥርዓት ማስቀረት እና መረጃዎቻችንን በራሳችን የዳታ ማዕከላት የማስተዳደር ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፤'' ሲሉ

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የፖሊሲ አማካሪው ኬልቪን ጂራጂ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፖድካስት፤ የቀደሙት አይነኬ የትራንስፖርት መስመሮች በአህጉሪቱ ንግድ ላይ ያሳደሩትን ተፅዕኖ፣ የሀገር ውስጥ እሴት ጨማሪ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሚና፣ በንግድ እንቅስቃሴ ወቅት የሚባክኑ የዶላር ወጪዎችን በቀጣናው የሀገር ውስጥ ገንዘቦች ክፍያ ሥርዓት (PAPSS) የመተካት ፋይዳ፣ እንዲሁም የዳታ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥና በሕዝብና በግል አጋርነት አማካኝነት ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ኮሪደሮችን በመገንባት አፍሪካን የ3 ትሪሊዮን ዶላር አንድ የጋራ ገበያ የማድረግ ስትራቴጂዎችን ከእንግዳችን ኬልቪን ጂራጂ ጋር በጥልቅ ዳስሰናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0