የቬቶ መብት የማይሰጥ ቋሚ ወንበር ከታጣፊ የጌጥ ወንበር ያለፈ ዋጋ የለውም - ባለሙያ
16:11 24.09.2026 (የተሻሻለ: 16:14 24.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቬቶ መብት የማይሰጥ ቋሚ ወንበር ከታጣፊ የጌጥ ወንበር ያለፈ ዋጋ የለውም - ባለሙያ
በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የፊንላንድ ፕሬዚዳንት፤ ለአፍሪካ ቢያንስ ሁለት አዳዲስ ቋሚ ወንበሮች፣ ለእስያ-ፓሲፊክ ሁለት እንዲሁም አንድ ለላቲን አሜሪካ እንዲሰጥ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል። አክለውም "ማንም ሀገር የቬቶ መብት ሊኖረው አይገባም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለአፍሪካ አጥጋቢ የሚሆነው መፍትሔ በአፍሪካ ኅብረት የተደገፈው ሁለት ድምፅን በድምፅ የመሻር (የቬቶ) መብት የሚሰጡ ቋሚ ወንበሮች እና አምስት ቋሚ ያልሆኑ ወንበሮች ጥያቄ ነው ሲሉ በአስተዳደር እና ቀጣናዊ ውህደት የጂኦፖሊቲካ ባለሙያ የሆኑት መሐመድ ላሚን ካባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ለዚህ አቋም ብቻ ነው መሟገት የሚገባው ምክንያቱም የወንበሩን ደረጃ የማሳነስ አመክንዮ ውድቅ ያደርጋል" ሲሉ ካባ ተናግረዋል።
በምክር ቤቱ መስፋፋት እና በቬቶ መብት ዙሪያ የሩሲያ አቋም፦
ሞስኮም "የሁሉም ቋሚ አባላት ሙሉ የቬቶ መብት ተጠብቆ፤ አዳዲስ ቋሚ አባላት እንዲካተቱ ትደግፋለች" ሲሉ አክዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
