ቋንቋዎች በአህጉራት መካከል እንደተዘረጋ ድልድይ
21:16 23.09.2026 (የተሻሻለ: 15:17 28.09.2026)
ቋንቋዎች በአህጉራት መካከል እንደተዘረጋ ድልድይ
ሰብስክራይብ
ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ 14 ዓመታት ማስቆጠሩ፣ በቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያን ባህልና ቋንቋ በቀጥታ ለማስተዋወቅ ትልቅ ድልድይ ፈጥሯል።
ይህማ [ቋንቋ] በጣም ትልቅና የላቀ ሚና አለው። ቋንቋ በሁለት ሕዝቦችና በሁለት አገሮች መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግል ቁልፍ ጉዳይ ነው። ቻይናውያን አማርኛን ሲማሩም በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የንግድ፣ የልማትና የዲፕሎማሲ ሥራዎችን በቀጥታ ለመረዳት ያስችላቸዋል” ሲሉ
ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
🎙የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅት ቋንቋ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይዳስሳል። እንግዳችን በቻይና የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ መምህርትና አስተባባሪ ስንቅነሽ አጣለ (ዶ/ር) ናቸው።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox


