- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የመስቀል በዓል፣ ሀገር በቀል የእርቅ ስርዓቶች እና የኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶች ለአፍሪካ የባህል ዲፕሎማሲ

የመስቀል በዓል፣ ሀገር በቀል የእርቅ ስርዓቶች እና የኢትዮጵያ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶች ለአፍሪካ የባህል ዲፕሎማሲ
ሰብስክራይብ

'የመስቀል በዓልና የደመራ ስነ-ስርዓት ተፈጥሮንና ማህበራዊ ህይወትን አናብቦ ይዞ የሚመጣ ህያው ባህላዊ ሀብታችን ነው። በዓሉ ከመከበሩ በፊት የሚከናወኑ ሀገር በቀል የእርቅና የይቅርታ ስርዓቶች፣ የዳያስፖራ ተመላሾች ትስስር እና በዩኔስኮ የተመዘገቡ ታላላቅ ቅርሶቻችንን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ጠብቆ ለዓለም ማስተዋወቅ ይገባናል።'' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የፎክሎር ተመራማሪ ዶክተር ፍሬሕይወት ባዩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ የመስቀል በዓል መንፈሳዊና ማህበራዊ ትርጉም፣ ሀገር በቀል የእርቅና የፍትህ ስርዓቶች፣ በዩኔስኮ የተመዘገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ፋይዳና እንክብካቤ፣ እንዲሁም እነዚህን ባህላዊ ሀብቶች ለደቡብ-ደቡብ የቱሪዝም ዲፕሎማሲ እና ለአህጉራዊ የእውቀት ሽግግር ማዋል በሚቻልበት ስትራቴጂ ላይ ከፎክሎር ተመራማሪዋ ዶክተር ፍሬሕይወት ባዩ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0