የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቃውንት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መማራቸው በጣም ከፍተኛ ጠቀሜታ ነበረው – መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል
17:19 23.09.2026 (የተሻሻለ: 19:44 23.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቃውንት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መማራቸው በጣም ከፍተኛ ጠቀሜታ ነበረው – መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል
ሊቃውንቱ ቤተ ክርስቲያንን በጥሩ ሁኔታ ያገለግላሉ፤ ሁሉም በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“በነገረ-መለኮት የዶክትሬት (ፒኤችዲ) ደረጃ ከፍተኛ ትምህርት አግኝተው ተመልሰዋል፤ በቤተ ክርስቲያኗም በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያገለግላሉ። ስለዚህ ስለ ሩሲያ ትክክለኛ እውቀት እንዲኖረን በጣም ጥሩ አገናኝ (ድልድይ) ሆነዋል፤ በእነዚህ ሰዎች አማካኝነት የተሳሳተ ወይም የተበላሸ እውቀት አይኖረንም።” ብለዋል፡፡
የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው “ለመላ ዓለም ሰላም” የተሰኘ የፎቶ ዐውደ–ርዕይ በአዲስ አበባ ለዕይታ ክፍት ሆኗል፡፡
መምህር ዳንኤል፣ "የሩሲያ የመንፈሳዊ ባሕል ቀናት በኢትዮጵያ" መርሃ-ግብር ወቅት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ልዑካን መካከል ከተደረገው የፓናል ውይይት ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች በቪዲዮው ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
