- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የቻይና-ሩሲያ ስትራቴጂካዊ ጥምረት፣ ባለብዙ-ወገን (Multipolar) ዓለም እና የአፍሪካ ሉዓላዊነት

የቻይና-ሩሲያ ስትራቴጂካዊ ጥምረት፣ ባለብዙ-ወገን (Multipolar) ዓለም እና የአፍሪካ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ

የቻይና እና የሩሲያ የተቀናጀ ጥምረት የምዕራባውያንን የአንድ ወገን የበላይነት በመቀየር፣ አዲስ ባለብዙ ወገን ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲገነባ ቀዳሚውን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ሁለቱ ሀገራት በሌሎች ሀገራት የውስጥ ፖለቲካና ሉዓላዊነት ላይ አለመግባታቸው እና የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ማጠናከራቸው ለአፍሪካና ለታዳጊ ሀገራት ያለ ፖለቲካዊ ጫና ልማታቸውን የሚያፋጥኑበት ትልቅ የነፃነት ምህዳር ፈጥሯል፤'' ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው ቶላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፖድካስት ክፍላችን፤ የቻይና እና ሩሲያ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ አጋርነት እያሳየ ያለውን ፈጣን እድገት፣ የምዕራባውያን ማዕቀቦች ውጤት አልባ መሆን፣ አፍሪካ ከእርዳታ ወጥታ ጥሬ ዕቃዎቿ ላይ እሴት በመጨመር እና ከቀረጥ ነፃ የንግድ እድሎችን በመጠቀም የምታገኘውን የኢኮኖሚ ነፃነት፣ በዶላር የበላይነት ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን እና የBRICS አዲሱን የልማት ባንክ መጠቀም፣ እንዲሁም ከቻይናና ሩሲያ በሚደረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር የአፍሪካን የዳታ ሉዓላዊነት የማረጋገጥና የኢትዮጵያ AI ተቋም ክፍለ-አህጉራዊ የማዕከልነት ሚና ላይ ከምሁሩ ዶ/ር ጌታቸው ቶላ ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ትንተና አጠቃለን ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0