የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ለሚገኙ 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሕይወት መቀየር መነሻ ሆኗል - ሚኒስቴሩ

ሰብስክራይብ

የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ለሚገኙ 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሕይወት መቀየር መነሻ ሆኗል - ሚኒስቴሩ

የከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔትና ምግብ ዋስትና ፕሮጀክት በ88 ከተሞች የሚገኙ ከ3 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ፕሮጀክቱን የሚመራው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 ድጋፉም ዕድሜ፣ ጾታ እና አካል ጉዳተኝነትን ሳይለይ ሁሉንም ያካተተ ነው።

🟠 ተጠቃሚዎች የእውቀት፣ የክህሎት እና የሥራ ባህል ባለቤት እንዲሆኑ አድርጓል።

🟠 መሥራት ለሚችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች በከተማ ጽዳት፣ አረንጓዴ ልማት እና መሠረተ ልማት ጥገና ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

🟠 ዜጎች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከመደገፍ ባለፈ ለሌሎች ወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ አቅም እየገነቡ ነው፡፡

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘው ቪዲዮ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የነበሩ ወጣቶችን ልዩ ልዩ የሥራ ላይ እንቅስቃሴ ያሳያል፡፡

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0