ኢትዮጵያ የስማርት ሕንፃ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት የሚያስችላትን የሥልጠና ማዕከል በይፋ አስመረቀች
15:10 21.09.2026 (የተሻሻለ: 15:14 21.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የስማርት ሕንፃ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት የሚያስችላትን የሥልጠና ማዕከል በይፋ አስመረቀች
ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን እና በዲጂታል ዘርፍ ዘመናዊ አሠራርን ለማስፋፋትና የዘመናዊ ሕንፃ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ልምድን ለማሳደግ የሚያስችላትን አዲስ የሥልጠና ማዕከል በአዲስ አበባ ሥራ አስጀምራለች።
የሥልጠና ማዕከሉ በሉባን ወርክሾፕ ማዕቀፍ በቻይና ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት እና በቻይና ኩባንያዎች በጋራ የተቋቋመ ነው።
ዋና ዋና አገልግሎቶች፦
🟠 የንድፈ-ሐሳብ ትምህርትን ከተግባራዊ የኢንጂነሪንግ ልምድ ጋር በቀጥታ ማያያዝ።
🟠 የስማርት ሕንፃዎችን የመረጃ መሰብሰቢያ ሴንሰሮች አሠራርና ቁጥጥር ማስተማር።
🟠 የሜካኒካል፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የኮምፒውተር ሥርዓቶች ውህደት የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን መተግበር።
🟠 የሕንፃዎችን አውቶሜሽን፣ ደህንነትና የተቀናጀ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋትና ማስተዳደር።
🟠 በሕንፃዎች ውስጥ የኤሌክትሪክ እና የኃይል አጠቃቀምን የሚቀንሱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መዘርጋት።
ማዕከሉ የ2026 የቻይና-አፍሪካ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዓመት ግቦችን ለማሳካትና በሙያ ትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ ተዘግቧ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
