የኢትዮጵያ የሥራ አጥነት ምጣኔ 12.3% ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ የሥራ አጥነት ምጣኔ 12
የኢትዮጵያ የሥራ አጥነት ምጣኔ 12 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.09.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የሥራ አጥነት ምጣኔ 12.3% ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ይፋ ባደረገው አዲስ መሠረት፤ በኢትዮጵያ መደበኛ የሥራ ስምሪት 53.9% እንዲሁም የሀገሪቱ አጠቃላይ የሥራ ስምሪት ምጣኔ 60.5% ደርሷል።

​

የጥናቱ ቁልፍ ነጥቦች፦

መደበኛ እና ኢመደበኛ ያልሆነ የሥራ ዘርፍ፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ መደበኛ የሥራ ስምሪት 53.9% ድርሻ በመያዝ ብልጫ ሲያሳይ፣ ኢመደበኛ የሥራ ስምሪት ደግሞ 44.2% ሆኖ ተመዝግቧል።

የከተማ እና የገጠር ንጽጽር፦ በከተሞች መደበኛ የሥራ ስምሪት 75.3% በማስመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ሲይዝ ኢመደበኛ ዘርፍ 22.8% ብቻ ነው። በአንጻሩ በገጠር አካባቢዎች ኢመደበኛ የሥራ ዘርፍ በ53.2% ላቀውን ድርሻ ሲወስድ፤ መደበኛ የሥራ ስምሪቱ 44.9% ነው።

አጠቃላይ የሥራ ስምሪት እና አጥነት፦ ብሔራዊ የሥራ ስምሪት ምጣኔ 60.5% ሲሆን የአጥነት መጠኑ 12.3% ነው። ቀሪው የኅብረተሰብ ክፍል ከሥራ ገበያ ውጪ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።

የክልሎች የሥራ አጥነት ምጣኔ ልዩነት

ከፍተኛ አጥነት፦ አዲስ አበባ 19.1% በማስመዝገብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛውን የአጥነት መጠን ስታስመዘግብ፤ ድሬዳዋ (14.5%)፣ ትግራይ (12.0%)፣ እና ኦሮሚያ (10.5%) ይከተላሉ።

ዝቅተኛ አጥነት፦ ዝቅተኛው የአጥነት መጠን የተመዘገበው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (4.4%) እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ (4.1%) ክልሎች ነው።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0