የዚምቧቤ ፕሬዚዳንት ከ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አስቀድሞ ለመተማመን እና አካታችነት ጥሪ አቀረቡ

© telegram sputnik_ethiopiaየዚምቧቤ ፕሬዚዳንት ከ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አስቀድሞ ለመተማመን እና አካታችነት ጥሪ አቀረቡ
የዚምቧቤ ፕሬዚዳንት ከ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አስቀድሞ ለመተማመን እና አካታችነት ጥሪ አቀረቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.09.2026
ሰብስክራይብ

የዚምቧቤ ፕሬዚዳንት ከ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አስቀድሞ ለመተማመን እና አካታችነት ጥሪ አቀረቡ

ኤመርሰን ምናንጋግዋ ይበልጥ የተሳሰረ፣ ጠንካራ እና አሳታፊ ዓለም እንዲገነባ ለዓለም መሪዎች ጥሪ በማቅረብ፤ በዚህ ዓመት ለሚካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ኒውዮርክ ገብተዋል።

ኤአይ እና የዲጂታል ትስስር፣ "በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ፈጣኑን ለውጥ" እያመጡ ባሉበት በዚህ ወቅት እምነት ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፤ "እምነትን መመለስ እና ለውጦችን መምራት" የሚለው የዘንድሮው መሪ ቃል ዓለም ያለችበትን የለውጥ ምዕራፍ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ምናንጋግዋ የዲጂታል ደህንነት፣ የግንኙነት ክፍተት ማጥበብ እና የኤአይ ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ ላይ በሚያተኩሩ ከፍተኛ ውይይቶች፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎች እና በዚምቧቤ ቢዝነስ ፎረም ላይ ይሳተፋሉ። ሐሙስ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አጠቃላይ ክርክር ላይ ንግግር ያደርጋሉም ተብሎ ይጠበቃል።

ከፕሬዚዳንቱ ጋር አብረው የተጓዙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሞን ሙርዊራ፤ ዚምቧቤ ግንኙነቷን ዳግም እያጠናከረች እና ለሰላም፣ ፍትሕ እና ለሀገራት እኩል ሉዓላዊነት በመቆም እ.ኤ.አ ከ2027 እስከ 2028 የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ ወንበርን ለመያዝ እየተዘጋጀች ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ዚምቧቤ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ለአፍሪካ ቋሚ ውክልና ለሚጠይቀው የኢዙልዊኒ ስምምነት ድጋፍ ሰጥታለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0