የኢትዮጵያና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፍተሻ ምዕራፍ ተጠናቀቀ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፍተሻ ምዕራፍ ተጠናቀቀ

በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ 100 ሜጋዋት የመብራት ኃይል ለማቅረብ የተካሄደው የስድስት ወራት የሙከራ ጊዜ መጠናቀቁን፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ገልጸዋል።

ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለመሸጋገር የሚቀሩ ጉዳዮችንም ኃላፊው ዘርዝረዋል፦

◾ በአቅርቦት መጠን፣ በታሪፍ ትግበራ፣ በቴክኒካዊ አሠራሮች ላይ መስማማት፣

◾ በኢትዮጵያ-ኬንያ የማስተላለፊያ መስመር እና በኬንያ-ታንዛኒያ አገናኝ የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚታዩ የአቅም ውስንነቶችን መፈታት።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከታንዛኒያ ባለሥልጣናት ጋር የሚደረገው ድርድር መቼ እንደሚጠናቀቅ አልገለጸም።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0