የኢትዮጵያ የአቮካዶ ማሳ ሽፋንን የማሳደግ ዕቅድ ትግበራ የት ደረሰ?

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የአቮካዶ ማሳ ሽፋንን የማሳደግ ዕቅድ ትግበራ የት ደረሰ?

ሀገሪቱ በብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም በ2032 ዓ.ም የአቮካዶ ማሳ ሽፋንን ወደ 192 ሺህ ሄክታር መሬት በማሳደግ፤ በዘርፉ ቀዳሚ የወጪ ንግድ ተዋናይ ለመሆን ጥረቷን አጠናክራለች።

ዕቅዱ ከ2018 ጥቅምት ወር ጀምሮ አፋርና ሶማሌን ሳይጨምር በ10 ክልሎች መተግበር ጀምሯል፡፡

እስካሁን የተመዘገቡ ውጤቶች፦

በ2018 ዓ.ም የአቮካዶ የመሬት ሽፋን 122 ሺህ 600 ሄክታር ደርሷል፣

ከ17 ሚሊዮን 267 ሺህ ኩንታል በላይ የምርት መጠን ተመዝግቧል።

የፕሮግራሙ ዐበይት ግቦች፦

የአቮካዶ ምርታማነትን ከ13.8 ኩንታል በሄክታር ወደ 23.4 ኩንታል ማሳደግ፣

የድህረ ምርት ብክነትን ከ41% ወደ 18% ዝቅ ማድረግ፣

ከ3 ሚሊዮን በላይ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ፣

299 አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0