የሚዲያ ዕድገት በዲጂታል እና በኤአይ ዘመን፦ በብራዛቪል የመረጃ፣ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ኤግዚቢሽን ተከፈተ
16:56 19.09.2026 (የተሻሻለ: 17:54 19.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሚዲያ ዕድገት በዲጂታል እና በኤአይ ዘመን፦ በብራዛቪል የመረጃ፣ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ኤግዚቢሽን ተከፈተ
ዘመናዊ ጋዜጠኞች ባሕላዊ የጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባርን ከአዳዲስ የዲጂታል ክህሎቶች ጋር ማጣመር አለባቸው። መረጃ ማመንጨት፣ ማረጋገጥ እና ሥነ-ምግባርን የመሳሰሉ መሰረታዊ ሙያዎችን ከዲጂታል መሳሪያዎች ጋር አጣጥመው መምራት ይኖርባቸዋል ሲሉ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ቲዬሪ ሌዛን ሙንጋላ የመረጃ፣ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ኤግዚቢሽን በተከፈተበት ወቅት ተናግረዋል።
ዝግጅቱ በኮንጎ ኪንቴሌ እስከ መስከረም 9 ድረስ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የኮንጎ የሚዲያ ባለሙያዎችን በማገናኘት ስለ ዘርፉ የዲጂታል ዕድገት በልዩ የፓነል ውይይቶች ይመክራሉ ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አናቶል ኮሊኔት ማኮሶ በበኩላቸው፤ ሕገ-መንግሥታዊ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ከፍተኛ ኃላፊነትን እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።
ማኅበራዊ ሚዲያ፣ ሀሰተኛ መረጃ እና ኤአይ በተስፋፋበት በዚህ ዘመን መረጃዎችን ማረጋገጥ እና እውነተኛ መረጃን ከአስተያየት መለየት ወሳኝ ነው ሲሉ ማኮሶ አክለው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia

© telegram sputnik_ethiopia
