ኬንያ ሚስጥራዊ የፀረ-ሽብር ጥቆማ መስጫ የስልክ መስመር ይፋ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopiaኬንያ ሚስጥራዊ የፀረ-ሽብር ጥቆማ መስጫ የስልክ መስመር ይፋ አደረገች
ኬንያ ሚስጥራዊ የፀረ-ሽብር ጥቆማ መስጫ የስልክ መስመር ይፋ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.09.2026
ሰብስክራይብ

ኬንያ ሚስጥራዊ የፀረ-ሽብር ጥቆማ መስጫ የስልክ መስመር ይፋ አደረገች

ነፃ የጥቆማ መስመሩ ኬንያውያን ያለ ምንም ስጋት ስለ አክራሪነት፣ ጽንፈኝነት እና ሽብርተኝነት በሚስጢር መረጃ እንዲያጋሩ ያስችላቸዋል ሲሉ የጠቅላይ ካቢኔ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ በናይሮቢ በተካሄደው ማስጀመሪያ ላይ ተናግረዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

ዓላማ፦ የጥቆማ መስመሩ ማኅበረሰቡ የደህንነት ተቋማት ቁልፍ አጋር እንዲሆን የሚያደርግና ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ እንቅፋቶችን የሚያስወግድ ነው።

የምርጫ ማስጠንቀቂያ፦ ሙዳቫዲ ከ2027ቱ ሀገራዊ ምርጫ አስቀድሞ የፖለቲካ ስብሰባዎች የጽንፈኛ ቡድኖች ዒላማ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሕዝቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢንተርኔት ስጋቶች፦ እየጨመሩ የመጡ የሳይበር ሽብርተኝነት እና እገታዎችን ለመከላከል ጥንቃቄው በኦንላይን ምህዳርም ሊጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ቀጣናዊ አለመረጋጋት፦ በአፍሪካ ቀንድ የሚታየው አለመረጋጋት የደህንነት ስጋቶችን ማባባሱን  በመቀጠሉ፤ የሕዝብ እና የደህንነት ተቋማት ትብብር ወሳኝ ነው።

የወንጀለኛ ቡድኖች ሽግግር፦ የተደራጁ የወንጀል ቡድኖች ጥብቅ ክትትል ካልተደረገባቸው ወደ ከባድ ጽንፈኛ እና የሽብር ድርጅትነት ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ አሳስበዋል።

ሙዳቫዲ መስመሩ ለፀረ-ሽብርተኝነት ጥቆማዎች እንጂ ለመደበኛ የፖሊስ አቤቱታ እንዳልተዘረጋ ገልጸው፤ ኬንያውያን በኃላፊነት እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0