የአፍሪካን ማንነት በሙዚቃ መጠበቅ 'በጣም ወሳኝ ነው' - ዛምቢያዊ ሙዚቀኛ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካን ማንነት በሙዚቃ መጠበቅ 'በጣም ወሳኝ ነው' - ዛምቢያዊ ሙዚቀኛ

 

"ከምንም በላይ እንደ ባሕላዊ ሀብት እቆጥረዋለሁ" ሲሉ ማቲው ቴምቦ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።

"አፍሮፖፕ" የሚለው ስያሜ የአፍሪካን የባሕል ብዝሃነት አሳንሶ ያሳያል ሲል የተቸው ቴምቦ፤ ይህም የአፍሪካ ሙዚቃ "በጣም ቀላል" እና በአብዛኛው "ምት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነው" ለሚለው የተሳሳተ አመለካከት አስተዋፅኦ ማድረጉንና አስተሳሰቡ እውነታውን እንደማያንፀባርቅ ገልጿል።

በአኀጉሪቷ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ብሔረሰቦች ይገኛሉ። በዛምቢያ ብቻ ወደ 70 የሚጠጉ፤ በኮንጎ ደግሞ ከዚያ በላይ አሉ። እያንዳንዱ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ልዩ የሙዚቃ ባሕል እያለው፤ ሁሉንም በአንድ አጠቃላይ ስያሜ መፈረጅ ትክክል አይደለም ሲል አፅንኦት ሰጥቷል።

"...የእኔ ዋና መልዕክት እርስ በርስ መከባበርን የተመለከተ ነው።...ሁላችንም አንድ የሰው ዘር ነን፤ እርስ በርሳችን ልንከባበር ይገባል። ብዝሃነታችንንም ልናከብር ይገባል" ብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0