ሩሲያ ሠር ጠመንጃዎች በአፍሪካ ቀዳሚ የመከላከያ ምርጫ እንደሆኑ ቀጥለዋል - ባለሙያ
14:37 19.09.2026 (የተሻሻለ: 14:44 19.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ሠር ጠመንጃዎች በአፍሪካ ቀዳሚ የመከላከያ ምርጫ እንደሆኑ ቀጥለዋል - ባለሙያ
የካላሽኒኮቭ ጠመንጃ ወሳኝ የመከላከያ መሣሪያ እና የታሪክ ምልክት በመሆኑ በመላው አፍሪካ አሁንም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው የሩሲያው ካላሽኒኮቭ ኩባንያ ባለሙያ ጊዮርጊ ጉቢች በደቡብ አፍሪካ ከተካሄደው የ2026 የአፍሪካ የኤሮስፔስና የመከላከያ ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
የኤኬ ጠመንጃ በመላው አፍሪካ በጣም ዝነኛ ከመሆኑ የተነሳ በአንዳንድ ሀገራት ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማዎች ላይ ጭምር እንዳረፈ ጠቁመዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ ለተወሰኑ የአፈሙዝ ዓይነች ያለው ፍላጎት እንደ የአኅጉሪቱ ቀጣና ይለያያል፦
▪ ሰሜን አፍሪካ፦ 5.56፣ 5.45 እና 7.62፣
▪ ማዕከላዊ አፍሪካ፦ 7.62፣
▪ ደቡብ አፍሪካ፦ 5.56።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
