ተጣብቀው የተወለዱ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በቀዶ ሕክምና ተለያዩ

ሰብስክራይብ

ተጣብቀው የተወለዱ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በቀዶ ሕክምና ተለያዩ

 

ጭንቅላታቸው ላይ ተጣብቀው የተወለዱት መንታ ሕፃናት በአሜሪካ ሚዙሪ ግዛት ሴንት ሉዊስ ከተማ በሚገኝ የሕፃናት ሆስፒታል 24 ሰዓታትን በፈጀ ውስብስብ እና ጥብቅ የቀዶ ጥገና ሕክምና በተሳካ ሁኔታ መለያየታቸው ተዘግቧል።

ህጻናቱ ህያብ እና ውህብቶ 300 ሰዓታት ገደማ ከወሰደ ዝርዝር ዕቅድ እና ዝግጅት በኋላ የካቲት 17 እና 18 ቀዶ ጥገናው እንደተደረገላቸው የሆስፒታሉ ኃላፊዎች ረቡዕ ይፋ አድርገዋል።

የሆስፒታሉ ዋና የህክምና ኃላፊ ዶ/ር አንድሪው ጄ ኋይት፤ "ጭንቅላታቸው ተያይዞ የተወለዱ መንትዮችን በቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ለመለየት እጅግ የላቀ ጥንቃቄ፣ ጥልቅ ትኩረት እና የበርካታ ህክምና ዘርፎች ቅንጅትን ይጠይቃል" ሲሉ የቀዶ ጥገና ህክምናውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።

የመንትዮቹ ህክምና በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በሮናልድ ማክዶናልድ ሀውስ በጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ እውን ሊሆን እንደቻለም ዘገባዎች ጠቁመዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0