ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ምርት በመላክ በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛውን ድርሻ ይዛለች - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ምርት በመላክ በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛውን ድርሻ ይዛለች - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

 

ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ በንግድ ቀጣናው የሚደረጉ ንግዶችን ለማቀላጠፍ በተዘጋጁ አዳዲስ መመሪያዎችና የዲጂታል ፖርታል ዙሪያ በተካሄደው መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ሀገሪቱ 23.6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን እንደላከች ገልጸዋል።

 

ውጤቱ አበረታች ቢሆንም ከአኅጉሪቱ የገበያ ትስስር በአግባቡ ተጠቃሚ እንዳይኮን እክል የሆኑ ተግዳሮቶችንም አንስተዋል፦

 

▪ ውስን የምርት ስብጥር፣

▪ በጥሬ ዕቃዎች ላይ ጥገኛ መሆን፣

▪ በግሉ ዘርፍ ውስጥ ያሉ የአቅም ውስንነቶች፣

▪ ተግባራዊ እና በቀላሉ ሊረዱ የሚችሉ የንግድ መረጃዎች አነስተኛ ተደራሽነት።

 

ኢትዮጵያ ከጥቅምት 30፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ በይፋ ዕቃዎችን መላክ መጀመሯ ይታወሳል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0