የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት አሠራሩን ሰው ሠራሽ አስተውህሎት መር አደረገ
17:05 17.09.2026 (የተሻሻለ: 17:14 17.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት አሠራሩን ሰው ሠራሽ አስተውህሎት መር አደረገ
አገልግሎቱ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የጭነት አስተላላፊዎች አሁናዊ የጊዜ የዋጋ ተመን እና የዲጂታል ቦታ ማስያዣ አቅሞችን በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ታግዞ ለማቅረብ ካርጎኤአይ ከተባለ የኤአይ ኩባንያ ጋር አጋርነት መሥርቷል።
ይህም በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ የሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ የጭነት አስተላላፊዎች ቀላል እና ፈጣን አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደረጀ ደረሮ፤ “ይህ እርምጃ ለፈጠራ ያለንን ቁርጠኝነት እና የዓለም አቀፉን የአየር ጭነት ኢንዱስትሪ እያደገ የመጣ ፍላጎት የሚያሟሉ ቀልጣፋና በመረጃ ላይ የተመሠረቱ መፍትሄዎችን ለማቅረብ የምናደርገውን ጥረት ያጠናክራል” ብለዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
