ትኩረቱን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ድርሳናት ጥናት ላይ ያደረገ ትምህርታዊ መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከፈተ
16:17 17.09.2026 (የተሻሻለ: 16:24 17.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ትኩረቱን በኢትዮጵያ ጥንታዊ ድርሳናት ጥናት ላይ ያደረገ ትምህርታዊ መድረክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከፈተ
መድረኩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ወዳጆች ማሕበር እና በቋንቋዎች እና ባሕል ጥናት ማዕከል ትብብር የተዘገጀ ሲሆን በዋናነት ድርሳናቱን ዲጂታይዝ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ስላሉ አሁናዊ ለውጦችና አዳዲስ ሁኔታዎች ዙሪያ የሚመክር ነው።
በመድረኩ እውቁ የታሪክ ምሁር ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ፣ የማኅበረሰብ ጥናት ባለሙያ ዶ/ር አሉላ ፓንክረስትን ጨምሮ የማኅበሩና የማዕከሉ አመራርና አባላት እንዲሁም የዘርፉ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ የማኅበረሰብ እና ባሕል ጥናት ባለሙያዎች መገኘታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
