የናይጄሪያ ጦር በዘመቻ ሀዲን ካይ ከ1 ሺህ 106 በላይ አሸባሪዎችን ደመሰሰ

የናይጄሪያ ጦር በዘመቻ ሀዲን ካይ ከ1 ሺህ 106 በላይ አሸባሪዎችን ደመሰሰ
የሀገሪቱ ጦር በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ትልቅ መሻሻሎች ማምጣቱን "የዘመቻ ሀዲን ካይ" የጋራ ግብረ-ኃይል ሰሜን ምስራቅ አዛዥ አብዱልሰላም አቡባከር በሥልጣን ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ወቅት ተናግረዋል።
አቡባከር የዘመቻ ሀዲን ካይ የተቀናጀ ዕዝን ማክሰኞ በዕዙ ዋና መምሪያ ለኢቢኩንሌ አጆሴ አስረክበዋል።
በቦርኖ ግዛት በሚገኙ ሁሉም የአካባቢ አስተዳደሮች ከሰባት ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ወደ ቀደመ ቀያቸው እንደተመለሱ እና ቀደም ሲል ተለቀው የነበሩ አካባቢዎችም እንደገና በነዋሪዎች መያዛቸውን አቡባከር ገልጸዋል።
የዘመቻውን ስኬቶች በተመለከተ አቡባከር ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገቡ ሌሎች ዋና ዋና ውጤቶችን እንደሚከትለው ገልፀዋል፡-
▪ ከ475 በላይ መሣሪያዎች እና 24 ሺህ 409 ዙር ጥይቶች ተወርሰዋል፣
▪ 295 በቤት ውስጥ የተሠሩ ፈንጂዎች ተገኝተው እንዲወድሙ ተደርገዋል፣
▪ ከአሸባሪዎች የፋይናንስ አቅርቦት ጋር በተያያዘ 200 ሺህ ዶላር በቁጥጥር ስር ውሏል፣
▪ 758 የአሸባሪዎች የሎጅስቲክስ ተባባሪዎች ተይዘዋል፣
▪ ከ969 በላይ የጃስ/ በምዕራባዊ አፍሪካ የኢስላሚክ ስቴት ክንፍ (ኢስዋፕ) ተዋጊዎች እና የቤተሰብ አባሎቻቸው እጃቸውን ሰጥተዋል፣
▪ 638 ሲቪሎች ከአሸባሪዎች እገታ ነፃ ወጥተል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
