ሞስኮ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ የአፍሪካን ውክልና በግንባር ቀደምትነት ትደግፋለች - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
17:35 16.09.2026 (የተሻሻለ: 17:44 16.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሞስኮ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ የአፍሪካን ውክልና በግንባር ቀደምትነት ትደግፋለች - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ምዕራባውያን ከበቂ በላይ የተወከሉ ሲሆን፣ እንደ አፍሪካ፣ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ያሉ ታደጊ ሀገራት ግን በቂ ውክልና እንደሌላቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በሩሲያእየተካሄደ በሚገኘው ዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ተናግረዋል።
እንደ ሕንድ እና ብራዚል ላሉ እጩዎች የቋሚ ወንበር መቀመጫ የሚሰጥ ማንኛውም ውሳኔ ከአፍሪካ ውክልና ጋር በተመሳሳይ እና በማንኛውም ሁኔታ መከናወን እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ሩሲያ የምዕራባውያን ቡድንን የሚወክሉ ማንኛቸውንም እጩዎች የማትደግፍ ሲሆን፣ የአፍሪካ አኀጉር ያገኘችው ንቁ አቋም ለአፍሪካ፣ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ወደ ተጨባጭ ፍትሕ እንዲቀየር ታደርጋለች ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
