የአፍሪካ ትልቁ የ2026 የኤሮስፔስ እና መከላከያ ኤክስፖ በደቡብ አፍሪካ ተከፈተ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ትልቁ የ2026 የኤሮስፔስ እና መከላከያ ኤክስፖ በደቡብ አፍሪካ ተከፈተ

13ኛው ዐውደ-ርዕይ በፕሪቶሪያ አቅራቢያ በሴንቹሪያን በሚገኘው "የወተርክሎፍ" አየር ኃይል ምድብ በዛሬው ዕለት የተከፈተ ሲሆን፣ እስከ እሁድ ይቆያል።

የዚህ ዓመት ትኩረት፦ የደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትር አንጂ ሞትሼጋ እንደገለጹት፣ የዘንድሮው ኤክስፖ ትኩረት የድሮን ስርዓቶች፣ የሳይበር ደህንነት እና ለመከላከያ ዘርፍ የሚያገለግል የሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ ነው።

ዓለም አቀፍ ተሳትፎ፦ ከአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ እንዲሁም ከሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ የተወጣጡ 33 ሀገራት እና 287 ኩባንያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ብለዋል ሚኒስትሯ።

የጎንዮሽ መርሃ ግብሮች፦ በወታደራዊ ልዑካን እና በመከላከያ ሚኒስትሮች መካከል ዋና ዋና የጦር መሣሪያዎች ግዥ ስምምነቶችን የሚያካትቱ ዝግ ድርድሮች፣ ዓለም አቀፍ ሲምፖዚየሞች እና ታክቲካዊ የጦር መሣሪያዎች ማሳያዎች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሩሲያ ተሳትፎ፦ የሀገሪቱ የወታደራዊ-ቴክኒክ ትብብር ፌዴራል አገልግሎት እንደገለጸው፣ ሩሲያ የሚከተሉትን ጨምሮ ወደ 500 የሚጠጉ ምርቶቿን በኤክስፖው ታሳየለች ተብሎ ይጠበቃል።

▪ ድሮኖች እና የድሮን መቃወሚያ ስርዓቶች፣

▪ የኤሌክትሮኒክስ የውጊያ ስርዓት፣

▪ ከአየር ወደ አየር የሚተኮሱ ሚሳኤሎች፣

▪ መሪ ያላቸው የአየር ላይ ቦምቦች እና መሪ የሌላቸው ሮኬቶች እንዲሁም

▪ የኤኬ ጠመንጃዎችን ጨምሮ አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0