አፍሪካውያን መሪዎች የምዕራባውያንን በዝባዥ ሥርዓት ለመቀየር ቁርጠኝነት እና የጋራ ድርድር ያስፈልጋቸዋል – ባለሙያ
08:25 15.09.2026 (የተሻሻለ: 08:34 15.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካውያን መሪዎች የምዕራባውያንን በዝባዥ ሥርዓት ለመቀየር ቁርጠኝነት እና የጋራ ድርድር ያስፈልጋቸዋል – ባለሙያ
አፍሪካን በአንድ አስተባብሮ መደራደር ይቻላል ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህሩ ዶ/ር ለታ ሲራ ከስፑትኒክ አፍሪካ "አፍሪካን ሃይትስ ሾው" ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
“አፍሪካ ትልቅ አሴት ናት፤ የራሷን እድል በራሷ መወሰን አለባት። ያላትን አቅም ተጠቀማ ከበዝባዦቹ ጋር እንደ አፍሪካ ሕብረት አንድ ሆና መደራደር ይኖርባታል።” ብለዋል፡፡
ባለሙያው ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
ቁርጠኝነትና ደፋር አመራር፦ አፍሪካውያን መሪዎች ነባሩን የበዝባዥነት አሰራር ለመቃወም እና ለመሞገት ጠንካራ ቁርጠኝነት ማሳየት አለባቸው።
የህዝብ ብዛትና የገበያ አቅም፦ እንደ ኢትዮጵያ (130 ሚሊዮን ህዝብ) ያሉ ሀገራት ያሏቸውን ትልቅ የህዝብ ቁጥርና የገበያ አቅም ለድርድር መጠቀሚያ ማድረግ ይችላሉ።
የጋራ ድርድር፦ አፍሪካውያን ሀገራት አምራች ሀገራት ምርታቸውን በፈለጉት መንገድ እንዳያራግፉባቸው በሕብረታቸው በኩል አንድ ሆነው መደራደር ይገባቸዋል።
የባለብዙ–ወገን አማራጭ ማጠናከር፦ የብሪክስ ስብስብ መጠናከር እና አፍሪካ ከቻይና እንዲሁም ከሩሲያ ጋር የምታደርገው ትብብር ለቀጣይ እድገት አዎንታዊ እርምጃ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X