- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ ካርታ አብዮት እና የመልክዓ-ምድራዊ ሉዓላዊነት

የአፍሪካ ካርታ አብዮት እና የመልክዓ-ምድራዊ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
''አሜሪካ አብዛኛውን ጊዜ ከአፍሪካ ወይም ከደቡብ ዓለም የሚመጡ ውሳኔዎችን እና ሃሳቦችን በመቃወም የምትታወቅ ሀገር ነች። የደቡብ ዓለም ድምፅ እየተሰማ በሄደ ቁጥር የምዕራባውያን የበላይነት እየተዋጠ የአፍሪካ ተፅዕኖ እያደገ እንደሚሄድ ስለሚታወቅ፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሃሳቡ መልካም ሆነ አልሆነ አሜሪካ የመቃወም ልማድ አላት፤'' ሲሉ የፖለቲካ እና አስተዳደር ምሁሩ ጂሬኛ ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በቶጎ አነሳሽነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቀረበው ረቂቅ ውሳኔ ላይ የተመዘገበውን የ164–1 ታሪካዊ የድምፅ ውሳኔ፣ የአሜሪካን በብቸኝነት ተነጥላ መቅረት፣ የሜርኬተር ካርታ ያደረሰውን ስነ-ልቦናዊ ተፅዕኖ፣ እንዲሁም አፍሪካ በትክክለኛው የእኩል ምድር ሞዴል በኩል የመልክዓ-ምድራዊ ሉዓላዊነቷን የምታረጋግጥበትን ስትራቴጂዎች ከምሁር ጂሬኛ ታደሰ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0