አፍሪካ የሚበዘብዟትን የምዕራባውያን ሀገራትና ተቋማት እርዳታ እና ብድር በቃ ማለት አለባት – ኢትዮጵያዊ የኢኮኖሚ ባለሙያ
20:25 14.09.2026 (የተሻሻለ: 20:34 14.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አፍሪካ የሚበዘብዟትን የምዕራባውያን ሀገራትና ተቋማት እርዳታ እና ብድር በቃ ማለት አለባት – ኢትዮጵያዊ የኢኮኖሚ ባለሙያ
የዓለም ባንክ፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና የሌሎችም የምዕራባውያን ተቋማትና ሀገራት ጥገኝነትን ውስት የሚያስገቡ ብድሮች እና እርዳታዎችን ማቆም እንደሚገባ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህሩ ዶ/ር ለታ ሲራ አሳስበዋል፡፡
“እርዳታ በቁሙ ሲታይ የሚጠቅም ይመስላል፤ ግን ጥገኝነትን ከመፍጠር፣ ሙስናንና የኑሮ ውድነትን ከማባባስ ባሻገር ለህዝቡ የሚያመጣው ጥቅም የለም። ስለዚህ የአፍሪካ አመራር አይሆንም ብሎ መቆም አለበት፤ ለሀገሬ የሚያዋጣኝን የማውቀው እኔ ነኝ ማለት አለበት፡፡” ብለዋል።
አፍሪካውያን መሪዎች እንደ ቡርኪና ፋሶ ባሉ ሀገራት እየታየ ያለውን እምቢተኝነት እንደ መልካም ተሞክሮ ሊወስዱ እንደሚገባም ባለሙያው ከስፑትኒክ አፍሪካ "አፍሪካን ሃይትስ ሾው" ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ ጠቁመዋል።
ዶ/ር ለታ አክለውም የውጭ ጫናዎችን እምቢ ማለት በጊዜያው ዋጋ ቢያስከፍልም፣ በረጅም ጊዜ ግን ለአኅጉሪቱ ዘላቂ እድገት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ አስረድተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X