ካዛኪስታን ለኢትዮጵያ ቡና እና አበቦች ንግድ አዲስ መግቢያ ልትሆን ነው

ሰብስክራይብ

ካዛኪስታን ለኢትዮጵያ ቡና እና አበቦች ንግድ አዲስ መግቢያ ልትሆን ነው

በኒው ዴልሂ ከተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካዛኪስታን ፕሬዝዳንት ቃሲም-ጆማርት ቶካየቭ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ካዛኪስታን የኢትዮጵያን ቡና፣ ሻይ እና አበቦች ወደ ሀገሯና ወደ ማዕከላዊ ኤስያ ገበያዎች የሚያሰራጭ የንግድ ማዕከል ለመክፈት ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ተስማምታለች።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 የካዛኪስታን የገበያ ፍላጎት፦ በቅርቡ (ሰኔ 2026) የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በካዛኪስታን የቡና ዋጋ ማሻቀብ ታይቷል። ሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ በውጭ ቡና ላይ ጥገኛ በመሆኗ የትራንስፖርት፣ የዋጋ ግሽበት እና የሠራተኛ ወጪዎች ዋጋውን ንረውባታል።

🟠 ዋጋ ማረጋጋት፦ ኢትዮጵያ የቡና፣ ሻይ እና አበባ ምርቶቿን በቀጥታ ወደ ካዛኪስታን መላክ መጀመሯ ለካዛኪስታን ገበያ የዋጋ መረጋጋትን ይዞላት ይመጣል፡፡

🟠 የኢትዮጵያ አዲስ ገበያ፦ ለኢትዮጵያ ወደ ካዛኪስታን እና ማዕከላዊ ኤስያ ሰፊ ገበያ ለመግባት ትልቅ የንግድ በር ይከፍትላታል። የቡና የወጪ ንግድን መዳረሻ የማስፋት ውጥንን ያፋጥንላታል፡፡

🟠 ስምምነት፦ ሁለቱ ሀገራት የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስሩን በተግባር ለማስጀመር የልዑካን ቡድኖችን ለመላክ ተስማምተዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0