አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም፦ "አፍሪካን ሃይትስ ሾው" በኢትዮ ኤፍኤም 108.7

ሰብስክራይብ

አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም፦ "አፍሪካን ሃይትስ ሾው" በኢትዮ ኤፍኤም 108.7

ስፑትኒክ አፍሪካ ከአኅጉራዊ ጉዳዮች እስከ ደቡባዊው ዓለም አጋርነት እና ጥልቅ የዜና ትንታኔዎች የሚዳስስ "አፍሪካን ሃይትስ ሾው" የተሰኘ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራሙን በኢትዮ ኤፍኤም 108.7 በይፋ ማስተላለፍ ጀመረ።

◾ የስርጭት ጊዜ፦ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ | ከምሽቱ 2፡00 እስከ 4፡00 ሠዓት

◾ የስርጭት ጣቢያ፦ ኢትዮ ኤፍኤም 108.7

የፕሮግራሙ ትኩረት፦

በዐበይት ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ላይ ከልማደኛ ዘገባዎች ወጣ ያሉ አዳዲስ ዕይታዎችን ማቅረብ

በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ ዋና ዋና ጂኦፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች

ለተለመዱት የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ተመራጭና ጥልቅ የዜና አማራጭ መሆን

"አዳዲስ ዕይታዎች ከጥልቅ ትንታኔ ጋር የሚገናኙበት" ይህ ፕሮግራም ታዋቂ የኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ ባለሙያዎችን በመጋበዝ የአፍሪካን እና የዓለምን ሁነቶች በጥልቀት ያቀርባል።

ስፑትኒክ አፍሪካ እ.አ.አ. ከመስከረም 1 ቀን 2026 ጀምሮ በኢትዮ ኤፍኤም የ6 ሠዓት ዕለታዊ የሬዲዮ ስርጭት መጀመሩ ይታወሳል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0