- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ጥበብ (አቡሻህር) እና የአፍሪካ የጊዜ ሉዓላዊነት

የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ጥበብ (አቡሻህር) እና የአፍሪካ የጊዜ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
''አቡሻህርና ባህረ ሀሳብ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ዘመናትን የሚቆጥር እንከን የለሽ የጥበብ መዛግብት ናቸው። አበቅቴና መጥቅን መነሻ አድርገን የምንቀምረው ስሌት የሃይማኖታዊ ስርዓት ማስፈጸሚያ ብቻ ሳይሆን፣ የጥልቅ እውቀት ህያው ማሳያ ነው።'' ሲሉ የአራቱ ጉባኤያት መምህር፣ ሊቀ ጠበብት (መጋቤ ሐዲስ) አማረ ተፈረደው ለተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ የአቡሻህርና የጥንተ ተፈጥሮ ስሌት፣ ቅኝ ግዛት በአፍሪካ የጊዜ መዋቅር ላይ ያደረሰውን ተፅዕኖ፣ የኢትዮጵያን የማይበገር የጊዜ ሉዓላዊነት፣ የቶጎን አህጉራዊ የቀን መቁጠሪያ እና የካርታ ማስተካከል እንቅስቃሴ እንዲሁም ሀገር በቀል የቀመር ጥበቦችን ለአፍሪካ የዕውቀት ሽግግር ማዋል በሚቻልበት ስትራቴጂ ላይ ከሊቀ ጠበብት አማረ ተፈረደው ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0