- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በኢትዮጵያ ጤና

ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በኢትዮጵያ ጤና
ሰብስክራይብ
''በዘውዲቱ ሆስፒታል የተሞከረው የካንሰር ዲቴክሽን እና ለቲቢ ህክምና የተሰራጩት AI ኤክስሬይ ማሽኖች ከ97% እስከ 98% ትክክለኛነት በማስመዝገብ፣ ከፍተኛ የስፔሻሊስት እጥረት ባለበት ሁኔታ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት አስችለዋል።'' ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ ገልጸዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በሀገር በቀል የAI ዲያግኖስቲክስ መፍትሔዎች የስፔሻሊስት ሐኪሞችን እጥረት የማጥበብ ሂደት፣ የጤና መረጃዎችን በሀገር ውስጥ የማስቀረት፣ የባለብዙ-ቋንቋ ዲጂታል መሳሪያዎች ሚና እና ኢትዮጵያ በ2030 የአፍሪካ የAI ማዕከል ለመሆን የምታደርገውን ስትራቴጂካዊ ጉዞ ከጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ እና ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0