የብሪክስ እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር የአፍሪካን የመደራደር አቅም እያሳደጉት ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየብሪክስ እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር የአፍሪካን የመደራደር አቅም እያሳደጉት ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
የብሪክስ እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር የአፍሪካን የመደራደር አቅም እያሳደጉት ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.09.2026
ሰብስክራይብ

የብሪክስ እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር የአፍሪካን የመደራደር አቅም እያሳደጉት ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ

 

የዓለም ንግድ እና ኢኮኖሚ ከምዕራባውያን ተፅዕኖ ወጥቶ ወደ ተለያዩ የንግድ ማዕከላት እየተቀየረ መሆኑን የንግድና ኢንቨስትመንት አማካሪው ከፈለኝ ሀይሉ ከስፑትኒክ አፍሪካ ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

ባለሙያው በቆይታቸው የብሪክስ እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር መስፋፋት እንዲሁም በምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም አማካኝነት በሚፈጠሩ አጋርነቶች ለአፍሪካ አዳዲስ የገበያ፣ የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት አማራጮችን እያቀረበ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

"የዓለም ንግድ ምዕራቡን ማዕከል ካደረገ ግሎባላይዜሽን፤ ብዝሃነት ወደ ነገሰበት ግሎባላይዜሽን እየተቀየረ ነው። ለአፍሪካ ዋናው ጥቅም ዶላርን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የምርጫ አማራጮችን ማስፋት ነው፤ ይሄ ደግሞ የአፍሪካን የመደራደር ሃይል ያሳድጋል።" ብለዋል፡፡

ከፈለኝ ኃይሉ፣ አፍሪካ ከአንድ አካል ጥገኝነት ወጥታ ከተለያዩ ሀገራት እና ቀጣናዎች ጋር በብዝኃ-አጋርነት መሥራት አለባት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0