- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የዩሬዢያ የንግድ ኮሪደሮች፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነት እና የአፍሪካ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ነፃነት

የዩሬዢያ የንግድ ኮሪደሮች፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነት እና የአፍሪካ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ነፃነት
ሰብስክራይብ
''የምስራቅ ኢኮኖሚክ ፎረም እና የዩሬዢያ አዳዲስ የንግድ ስምምነቶች ከአትላንቲክ ውጭ ያሉ የበለፀጉ የንግድ ኮሪደሮች እንዲፈጠሩ እያደረጉ ነው። አፍሪካ በBRICS+ እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር ማዕቀፍ ውስጥ የምዕራባውያንን የፋይናንስ የበላይነት እና የዶላር ጥገኝነት ቀልብሳ የራሷን የፋይናንስና የንግድ ነፃነት እንድታረጋግጥ እና አዳዲስ ዕድሎችን እንድታገኝ የሚያስችላት ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ምዕራፍ ተከፍቷል'' ሲሉ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በቭላዲቮስቶክ እየተካሄደ የሚገኘውን 11ኛውን የምስራቅ ኢኮኖሚክ ፎረም መነሻ በማድረግ፣ ሩሲያ ወደ እስያ-ፓሲፊክ የምታደርገውን የንግድ አቅጣጫ ለውጥ፣ የምዕራባውያንን SWIFT ለመተካት የታለመውን አዲሱን ‘የምስራቅ ፋይናንስ ማዕከል’ (Eastern Financial Centre)፣ የሲቪል ኑክሌር ኃይል ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ እሴት ጭማሪ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ፣ እንዲሁም በፎረሙ ላይ የተንጸባረቁትን የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢንዶኔዥያው ፕሬዝደንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ ታሪካዊ መግለጫዎች ከቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0